ለብዙ ዘመናት የሀገራችን ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከመንግስት ጋር በመቆራኘቱ የተነሳ የግል ኢኮኖሚ ዘርፉ ብዙም አላደገም። ለዚህም ይሆናል አብዛኛው ሰው የራሱን ስራ ከመፍጠር ይልቅ በመንግስት ተቋማት ስራ ሲፈልግ የሚውለው። በስደት በምንኖርበት አገርም ትኩረታችን ወደግል ተቋማት ዞሮ እንደሆን እንጅ ያው ተቀጥሮ ለመስራት ያለን ፍላጎት አልተቀየረም። የዛሬው ፊቸር ጽሁፍ አላማም የራስን ቢዝነስ ለመጀመር እንዲቻል አቅጣጫ ማሳየት ነው።