ቅዳሜ ገበያ Denver September 2024
October 31, 2024የቅዳሜ ገበያን ህትመት የዛሬ ሁለት ዓመት ስንጀምር ራዕያችን በጣም ሰፊ ነበር። ከዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮ ውጭ የተሳካልን በዴንቨር በመሆኑ ለዴንቨር የንግድ ተቋማትና አንባቢያን ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን። አሁን ደግሞ የቅዳሜ ገበያ አሳታሚ ተቋማችን ስር እየሰደደችና አገልግሎቷ እየሰፋ ይገኛል። ማራኪ ማስታዎቂያ፤ ማራኪ ቲቪ፤ ማራኪ ስቶር፤ ማራኪ ሲቲ፤ ማራኪ የቢዝንስና የፋይናንስ አገልግሎት ማቅረቢያ፤ ማራኪ የሙያ ክህሎት ማስጨበጫና ስራ አፈላላጊ ወዘተ ወደስራ እየገቡ ነው። ለዚህም ስኬት ከጎናችን የተሰለፉትን እያመሰገንን በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ እንዲሁም የቢዝነስ ባለቤት የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን። በሚቀጥለው ዓመትም ማራኪ የህዝብ ተቋም እንድትሆን እየሰራን ነው። መጭው ዘመን ለማራኪና አባላቱ የሰኬት ዘመን እንደሚሆን አንጠራጠርም።